Tuesday, October 08, 2013

«ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት በአንድ የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት ላይ ብቻ የሚመሠረት አይሆንም» - ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

(Oct 08, 2013, (አዲስ አበባ))--ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ዓርብ ከመገናኛ ብዙኃን ለቀረቡላቸው ሀገራዊ፣ አካባቢያዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቀረቡት ጥያቄዎችና ከሰጧቸው ምላሾች መካከል ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸውን በኢኮኖሚ ገጻችን ማቅረብ መጀመራችን ይታወቃል። ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ደግሞ እነሆ በእዚህ ገጽ ይዘን ቀርበናል።

በቅድሚያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀድ መው ለመነሻ እንዲሆኑ ብለው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ፖለቲካዊ መልክ ያላቸ ውን እናቀርባለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፡- በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ አካባቢያችን ለአሸባ ሪዎች ጥቃት የተጋለጠ አካባቢ ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ የአገራችንን ሰላምና ፀጥታ አስከብረናል፡፡ያም ሆኖ አሁንም ከአሸባሪዎች ጥቃት ራሳችንን መከላከል ይኖርብናል። ማንኛችንም ከአሸባሪዎች ጥቃት ነፃ ልንሆን ስለማንችልም ከመላው የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ጋርም በትብብርና በጋራ በመስራት አሽባሪዎችን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው፡፡ የአገራችን ሰላምና ፀጥታ ተከብሮ ዓመቱ አልፏል፤ በተያዘው አመትም በተመሳሳይ ሁኔታ ለልማታችን እንቅፋት እንዳይሆን በሚሆን ደረጃ ሰላምና ፀጥታን ለመጠበቅ ተዘጋጅተናል፡፡ስለዚህ ለብቻችን ሳይሆን ከአካባቢው አገራት ጋር በተቀናጀ መንገድ ለመስራት የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ጎረቤቶቻችንን በተመለከተ ከኤርትራ በስተቀር ከሌሎቹ ጎረቤት አገሮቻችን ጋር ስትራቴጂካዊ የሆነ ግንኙነት አለን፡፡ ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከፍተኛ ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡በእዚህም ውጤታማ ተግባሮች ተከናውነዋል ማለት ይቻላል፡፡

በተለይ በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን በሚደ ረገው ጥረት በአካባቢዋ የሚከሰቱትን አለመግባባቶች በድርድር ለመፍታትና በተለያዩ የሶማሊያ ኃይሎች በተለይም የክልልና የፌዴራል መንግሥት ኃይሎች ተቀናጅተው ሊሠሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርገን የተሳኩ ተግባሮችን አከናው ነናል፡፡በተመሳሳይ አልሸባብን ለመዋጋት ከአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም)፣ ከሶማሊያ ኃይል፣ የደህንነት ኃይሎች ጋር እንደዚሁም ከሌሎች ዓለም አቀፍ በሶማሊያ ላይ ያገባኛል ከሚሉ ኃይሎች ጋር በመተባበር በእዚህ አካባቢ ሰላም ለማስፈን የተከናወኑ ተግባሮች የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትን በማገዝ ውጤቶች የተገኙበት እንደሆነ ይታወቃል።

በሱዳንና ደቡብ ሱዳን በቅርቡም እንዳያ ችሁት ሁለቱ አገሮች በኢጋድ ማዕቀፍ ውስጥ ያደረጉትን ስምምነት በአግባቡ እንዲተገብሩ ባደረግነው ጥረት በመካከላቸው የነበረውን ቁርሾ በማስቀረት ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው ወደፊት ለማስቀጠል ተስማምተዋል። የኢት ዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይልም በአቢዬ ሥራውን በተገቢው ሁኔታ እየተወጣ ነው፡፡ ስለዚህም በእነዚህም አገሮች ያለው ሰላም በጋራ ለሰላም በምናደርው ሥራችን ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደመሆኑ መጠን ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀ ሳቀስን እንገኛለን፡፡

ከኬንያ፣ ከሱዳንና ከደቡብ ሱዳን ጋር የተለየ ስምምነት ባለፈው ዓመት ተፈራር መናል፡፡ ይኼ የተለየ ስምምነት ጎረቤት አገሮች እርስ በእርስ የሚሠሩበት በንግድ፣ በኢንቨ ስትመንት፣ በመሠረተ ልማት የሚተሳሰሩበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡ይኼም ለዘላቂ ሰላማችን እጅግ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ስትራቴ ጂካዊ ግንኙነታችን የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

በሌላም በኩል ጅቡቲ በኢኮኖሚ መሠረተ ልማታችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምታበረክት አገር ናት፡፡ስለዚህ ከጅቡቲ ጋር ከእዚህ ቀደም የተፈራረምነውን ልዩ ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ የተሳካ ሥራ አሁንም ቀጥለናል፡፡

ከባለ ብዙ ወገኖች ግንኙነት ኢትዮጵያ አፍሪካን ወክላ ባለፈው ዓመት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካ ኅብረት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት በጥሩ ሁኔታ አክብረናል፡፡በዓል ብቻ የተከበረበት አልነበረም። አፍሪካ በሚቀጥሉት 50 ዓመት ጉዞዋ ምን መሆን አለባት የሚል ስትራቴጂያዊ ሰነድ ዝግጅት ሲካሄድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና ተጫውታ ለች፡፡ይኼ አፍሪካ አሁን የጀመረችውን የልማትና የዕድገት እንቅስቃሴ የበለጠ ለማቀላጠፍ የሚያስችል ሁኔታ ይፈጥርልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ከእዚህ ባሻገር በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አፍሪካ ኅብረትና ኢትዮጵያንም በመወከል የአፍሪካን ድምፅ ለማሰማት ከፍተኛ ጥረት አድርገናል፡፡ይኼ እንግዲህ የተሳካ ነው ብሎ መውሰድ ይቻ ላል፡፡ ዓመቱ በባለ ብዙ ወገኖች ግንኙነትም አገራችን የምታደርገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የቀጠለበት ዓመት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ጥያቄ፡- በቅርቡ የኤርትራው ፕሬዚዳ ንት ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግደብ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል። ይህን የፕሬዚዳ ንቱን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት እንዴት ያየዋል? እስከ አሁን ድረስ ከኤርትራ ጋር የተፈጠረውን ልዩነት ለማርገብ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አልተጀ መረም ወይ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፡- የኤርትራ መንግሥትን በተመለከተ ከኤርትራ መንግሥት ጋር የተሻሻለ ወይም የተለወጠ ግንኙነት የለም። ባለበት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ከእዚያ ባሻገር «የኤርትራው ፕሬዚዳንት ከኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት ጥያቄ ወይም ሃሳብ አቅርበዋል» ለሚለው እንግዲህ የእርሳቸው ሃሳብ ነው የሚሆነው። በእኛ እምነት ከኤርትራ ጋር ያለን ግንኙነት በአንድ የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት ላይ ብቻ የሚመሠረት አይሆንም፤ ከእዚያ በላይ ግንኙነት ማድረግ እንችላለን። በጣም ጎረቤቶች ነን። ከጎረቤትነትም በላይ ደግሞ በብዙ ነገሮች የምንገናኝ የምንተሳሰር ሕዝቦች ነን። ስለዚህ ከኤርትራ ጋር ያለንን ግንኙነት በማሻሻል ወይም ወደ መደበኛው ሁኔታ በመመለስ ወደ ጥሩ ጉርብትና ለማድረስ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች።ይህ ጥረቷ እስከ አሁን ድረስ ምላሽ ያላገኘው የኤርትራ ሥርዓት ለእዚህ የተዘጋጀ ባለመሆኑ ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት ጀምሮ በጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ እየጠበቀ ያለበት ሁኔታ አለ። ስለዚህ አሁን ሁኔታዎችን ለማሻሻል ፈቃደኛ ከሆኑ መልካም ነው። ነገር ግን የኤርትራ መንግሥት በባህሪው በእዚህ ደረጃ የሚታይ አይደለም። አሁን አጣብቂኝ ውስጥ የገባ መሆኑን የሚያሳይ ኑዛዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኑዛዜው የሚያመጣው ለውጥ ካለ ወደፊት የምናየው ይሆናል። አሁን ባለው ደረጃ የረባ ነገር አለ ብሎ መውሰድ ያስቸግራል። ስለዚህ በእዚህ ደረጃ ቢታይ የተሻለ ይሆናል።

የኢትዮጵያ አቋም የዛሬ ዘጠኝ ዓመት የተያዘ አቋም ነው፤ ዛሬ ነገም ይኸው ነው የሚሆነው። ስለዚህ ኳሱ በእነርሱ እጅ እንዳለ ከእዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ገልጸናል። ይልቅ «ለራሷ ባልሆነ ክንፍ ሌላውን ልትሸፍን እንደምትፈልግ አሞራ ለራሱ መሆን ያቃተው መንግሥት ሌሎችን እደግፋለሁ» እያለ ደፋ ቀን ማለቱ የኪሳራ ምልክት እንደሆነ ያመለክታል።

ያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ደግሞ የሚያቀርቧቸው ሃሳቦች አሉ። እነዚህ ደግሞ በራሱ አቅም የሌለው አካል ሌላውን እደግፋለሁ እያለ የሚያስባ ቸው ደካማ የሆኑ አስተሳሰቦችን በተለያዩ ጊዜያት እንሰማለን። የቤት ሥራቸውን ባግባቡ ቢሠሩና ራሳቸውንና መንግሥታቸውን በትክክለኛው ጎዳና ቢያቆሙ ለአካባቢው ሕዝብም፣ ለአፍሪካም፣ ለአፍሪካ ቀንድም ለሁሉም ጠቃሚ ይሆናል የሚል እምነት አለን።ስለዚህ ኢትዮጵያ በሰላም አጀንዳ ላይ ሁልጊዜ ጽኑና ቋሚ አቋም ያላት ሀገር እንደሆነች በእዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ 

No comments:

Post a Comment