(July 27, 2013, ( ኢሬቴድ))--የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካ ላይ በሚካሄደውን የቻን ውድድር ለማለፍ የሩዋንዳ አቻውን ኪጋሊላይ በመለያ ምት 6 ለ 5 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በመጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በአስራት መገርሳ ብቸኛ ጎል የሩዋንዳ አቻውን 1 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋሊያዎቹ የተሻለ እድል ይዘው ነበር ወደ ኪጋሊ የተጓዙት።በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ የጨዋታ እንቅስቃሴ የነበራቸው ዋሊያዎቹ ተጨማሪ ጎል ማስቆጠር ሳይችሉ 0 ለ 0 የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል።
በሁለተኛ አጋማሽ ተመጣጣኝ የሆነ ፉክክር ያደረጉ ሲሆን በ68ኛው ደቂቃ ዋሊያዎቹን ያስደነገጠ ጎል ሩዋንዳዎች አስቆጥረው ጨዋታው በአጠቃላይ 1 ለ 1 በሆነ ውጤት 90ው ደቂቃ ተጠናቋል።
ሁለቱን ሀገሮች ለመለየት በተደረገው የመለያ ምት ዋሊያዎቹ 6ለ5 በሆነ ውጤት የደቡብ አፍሪካ ጉዟቸውን አሳክተዋል ። በፍጹም ቅጣት ምቱ የግብ ጠባቂው ሲሳይ ባንጫ ድንቅ ብቃት የታየበት ነበር።
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:
Post a Comment