Wednesday, July 24, 2013

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከዩቲዩብ ታገደ የተባለው ሃሰት ነው

(July 24, 2013, (አዲስ አበባ))በማህበራዊ ድረ ገፆች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከዩቲዩብ ቻነል እንደታገደ ተደርጎ የተሰራጨው ዘገባ ሃሰት መሆኑን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ገለፀ፡፡

ድርጅቱ ኢትዮጵያን ቲቪ /Ethiopiantv/ የሚል ዌብሳይት እንደሌለው ገልፆ ድርጅቱ የሚጠቀመው www.ertagov.com በሚል አድራሻ የሚታወቀውን የድርጅቱን ዌብሳይትና www.facebook.com/ertanews በሚል ሊንክ የሚገኘውን የፌስቡክ ገፅ ብቻ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

ከዚህ ውጭ ያሉት በድርጅቱ ስም የተከፈቱ ዌብሳይቶችም ሆኑ ማህበራዊ ድረ ገፆች እንደማይወክሉት ገልጧል፡፡ ኢሬቴድ እስካሁን ድረስ በዩቲዩብ በኩል የሚጭነው ዝግጅት እንዳልነበረው ገልፆ በቅርቡ ግን ከዩ ቲዩብ ጋር ስምምነት በማድረግ በራሱ የሚያዘጋጃቸውን ቪዲዮዎች ለደንበኞቹ እንደሚያደርስ አስታውቋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በኢሬቴድ የሚዘጋጁ ዜናዎችን፤ ፕሮግራሞችንና የመዝናኛ ዝግጅቶችን ከላይ በተጠቀሱት ሳይቶች ደንበኞቹ እንዲከታተሉ ጋብዟል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment