(ሜይ, 03, 2013, ቅዳሜ ))--የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳዔ በዓል ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመንከባከብ መሆን እንደሚገባ የኃይማኖት መሪዎች አሳሰቡ፡፡ ምዕመኑ በሀገር ልማት ላይ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ምዕመኑ ርብርቡን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡
በዓሉንም በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንዳሉት የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰው ልጅና በእግዜአብሄር መካከል እርቅ የተደረገበት ነው፡፡
በዓሉ ስናከብር እርስ በእርሳችን ልንፋቀር እና ልንዋደድ ይገባል ያሉት አቡነ ማትያስ በዓሉንም የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በመንከባከብ ልናሳልፍ እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡ ብጹዕ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የተገኘውን መሰረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቄስ ዶክተር ዋቅ ስዩም ኢዶሳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዘዳንት ትንሳኤው በእግዜአብሄር በሰው ልጆች መካከል የነበረው የጥል ጉድጓድ የፈረሰበት ነው ብለዋል፡፡ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው በሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን የዜጎች ሰቆቃ እያበረከተ ያለውን ህገ ወጥ ስደት ለመግታት መመካከር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትን በመወከል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የህብረቱ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ህሩይ ጽጌ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሰው ልጅ ደህንነትን አግኝቷል፡፡
በበዓሉም እርዳታ የሚሹ ወገኖችን የምናስብበት በልማት ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የምናጎለብትበት ሊሆን ይገባል፡፡ በሀገራችን በተጀመሩ የልማት ስራዎችም ህበረተሰቡ እያደረገ ያለውን ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የኃይማኖት መሪዎች በመልዕክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

No comments:
Post a Comment