(Apr 14, 2103, (አዲሰ
አበባ))--ኢትዮጵያውያን ዘማቾች ለኮሪያ የከፈሉት መስዋዕትነት በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ወዳጅነት በፅኑ መሠረት ላይ እንዲገነባ አድርጎታል፤ ኢትዮጵያውያን ዘማቾች ለኮሪያ የከፈሉት መስዋዕትነት በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለውን ወዳጅነት በፅኑ መሠረት ላይ እንዲገነባ አድርጎታል፤
ኢትዮጵያ ከ62 ዓመት በፊት በኮሪያ ግንባር የመጀመሪያዋ የሆነውን ዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ግዴታዋን የተወጣችበት መታሰቢያ በዓል ተከበረ። ትናንት የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ግቢ ውስጥ በዓሉ በተከበረበት ወቅት ፕሬዘዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በተወካያቸው አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ በዓለም ላይ ሰላምን በማስከበር ረገድ ከ62 ዓመት በፊት በኮሪያ ምድር የተፈጸመው ጀብዱ አሁን ላለው የሰላም ተግባር ፈር ቀዳጅ ነው።
በኮሪያ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ወታደሮች በተካፈሉባቸው 238 ውጊያዎች ሳይሸነፉ መውጣታቸው፣ ለጠላት እጅ አለመስጠታቸው፣ በጦርነቱ ከተካፈሉት 16 አገሮች አኳያ 122 ወታደሮች ብቻ መሰዋታቸውና 536 ብቻ መቁሰላቸው በጠላት ዘንድ «ኢትዮጵያውያን ከሰው ፍጡር በላይ ናቸው አስብሏል» ብለዋል።
አሁንም ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷና ነፃነቷን
ከማስከበር አልፋ በዓለም ሰላም እንዲሰፍን የሚያስችላትን ተልዕኮ በመወጣት ላይ እንደምትገኝ አስታውሰው፤ ከኮሪያ
በኋላ በተለይም በአፍሪካ ሰላም በማስከበር ተሠማርታ ግዳጇን በሚገባ እየተወጣች መሆኗን ጠቁመዋል ።
የኮሪያ ዘማቾች ኢትዮጵያውያን ማህበር ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መለሰ ተሰማ እንደተናገሩት፤ የመታሰቢያ በዓሉ የሚከበረው ኢትዮጵያውያን ወደ ኮሪያ የዘመቱበትን62ኛ ዓመትና በጦርነቱ የተሰዉ 122 ጀግኖችን ለማስታወስ ነው። «ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም መከበር ከኮሪያ ዘመቻ አንስቶ ዓለም አቀፍ ግዴታዋን እየተወጣች ነው» ብለዋል።
በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ጀንግ ጊቶን ኪም በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያውያን ከአፍሪካ ብቸኛ የኮሪያ ጦርነት ተሳታፊ ወገኖች ናቸው። ከ62 ዓመት በፊት ለነፃነቷና ሰላሟ ደማቸውን ያፈሰሱላት ኮሪያ ዛሬ ያደገች አገር ልትሆን ችላለች።
በኮሪያና በኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል
ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ በመምጣቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ወደ ሴኡል እንዲበርር
ለማስቻል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ይህም የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች ትስስርና ግንኙነት ይበልጥ
እንደሚያጠናክረው ጠቁመዋል።
አያይዘውም የኮሪያ መንግሥት በሚያደርገው እርዳታ 60 ያህል የዘማች ልጆች በኮሪያ የሥራ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረዋል። «የኢትዮጵያውያን ውለታ በሕዝባችን ልብ ውስጥ ለዘላለም ይኖራል።» ያሉት አምባሳደሩ፤ አገሪቷ ድህነትን ለመዋጋት በምታደርገው እንቅስቃሴ ኮሪያ ድጋፏን እንደምታደርግ ተናግረዋል።
«ሁልጊዜም ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት እንዲሁም ከዘማች ቤተሰቦች ጋር የኮሪያ መንግስት እንዳለ እንዳትዘነጉ» ሲሉ ተናግረዋል ።
ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ
«ሁልጊዜም ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት እንዲሁም ከዘማች ቤተሰቦች ጋር የኮሪያ መንግስት እንዳለ እንዳትዘነጉ» ሲሉ ተናግረዋል ።
ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment