Sunday, March 24, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቦትሱዋናን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

(መጋቢት 15/2005, (አዲሰ አበባ))--የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቦስትዋና ጋር ባደረገው ጨዋታ አንድ ለባዶ አሸነፈ። ቡድኑ ለአሸናፊነት የምታበቃውን ግብ በ89ነኛው ደቂቃ ለደደቢት ክለብ በሚጫወተው አጥቂ ጌታነህ ከበደ አማካይነት አስቆጥሯል። 



ቡድኑ ያለበትን ምድብ በሰባት ነጥብና በሦስት ግቦች በማስመዝገብ መሪነቱን ለመያዝም በቅቷል። አብዛኛው የጨዋታውን ጊዜ በበላይነት የተቆጣጠረው ቡድን ሊገቡ የሚችሉ በርካታ ኳሶችም መክነውበታል። የቦትስዋና ብሄራዊ ቡድን አልፎ አልፎ አደገኛ ሙከራዎችን ሲያደርግም ታይቷል።

ጨዋታውን በአዲስ አበባ ስታዲዬምና በመገናኛ ብዙኃን የተከታተለው ሕዝብም ደስታውን በመግለጽ ላይ ነው። እንደ አውሮፓውያን በ2014 በምታስተናግደው ምድብ ውስጥ ደቡብ አፍሪካ፣ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ቦትስዋና ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ኢዜአ አስታውሷል። 

በምድቡ እስካሁን ሦስት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፣ኢትዮጵያ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ከቦትስዋና ጋር የመልስ ጨዋታዎች አላት። በአዲስ አበባ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ትጋጠማለች። 
ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

Related topics: 
ዋልያዎቹ እሁድ ቦትስዋናን ያስተናግዳሉ
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሃያ ሁለት ተጫዋቾች ተመረጡ 
«ለቡድኑ ሽንፈት ተጠያቂው እኔ ነኝ»- አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው
«ዋሊያዎቹ በጣም ፈትነውን ነበር»- አህመድ ሙሳ  
Home    

No comments:

Post a Comment