Wednesday, March 06, 2013

በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ረቂቅ ተዘጋጀ

(Mar 06, 2013, አዲስ አበባ)--በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር ጥረትን በተቀናጀ አኳኋን ለመፈጸም የሚያስችል በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ረቂቅ ተዘጋጀ።

ይኸው ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሦስት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋርም በሂልተን ሆቴል ምክክር ተደርጎበታል። የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ በሕገ-መንግሥቱ የሰፈሩትን መብቶች በማክበርና በማስከበር ረገድ እስካሁን በርካታ ሥራዎች የተከናወኑ ቢሆንም ጥረቶቹ ወጥ በሆነ የድርጊት መርሐ ግብር የሚመሩ አልነበሩም።

ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ የፌዴራልና የክልል ተቋማት በተናጠል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጭ የራሱ ዕቅድ ወጥቶለት የሚፈጸምና በዕቅዱ መሰረትም እየተገመገመና እየተለካ ሲመራ የቆየ አይደለም።

የድርጊት መርሐ ግብሩ የተለያዩ መንግሥታዊ አካላት ሰብዓዊ መብቶችን በማስከበር ረገድ ከዚህ ቀደም በተናጠል ያደርጉት የነበረውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ አኳኋን እንዲያከናውኑ የሚያደርግ አዲስ ዕቅድ ነው ብለዋል። እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፤ ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብሩ ተቋማቱ የሚመሩበትን አካሄድና አቅጣጫም የሚያስቀጥ ነው። በአገሪቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት አጠባበቅ እንዲዳብርና እንዲጎለብት ከማድረጉም ባሻገር የዴሞክራሲየመልካም አስተዳደር ግንባታውን ይበልጥ የሚያፋጥን ይሆናል።

-መንግሥቱ የተረጋገጡትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አተገባበር ይበልጥ እየተጠናከረና እያደገ የሚሄድበትን ሁኔታም ያመቻቻል። ይህ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች የድርጊት መርሐ ግብር ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ጋር አብሮ ተፈፃሚ እንደሚሆንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
 
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምሳደር ጥሩነህ ዜና በበኩላቸውአዲሱ ሠነድ መንግሥት -መንግሥታዊ ዋስትና ያገኙትን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመጠበቅና በማረጋገጥ ረገድ ያለውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው።

መርሐ ግብሩን የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ከሚመለከታቸው የልማት አጋሮች ፣ ከሲቪል ማህበራትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሚፈጽሙት ነው ብለዋል። አምባሳደር ጥሩነህ እንዳሉትየብሔራዊ የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሐ ግብር ማዘጋጀትና መተግበር በዓለም አቀፍ ደረጃ መግባባት የተፈጠረበት ጉዳይ መፈጸምና ዓለም አቀፍ ኃላፊነትን መወጣት ጭምር ነው።

ለውይይት የቀረበው አዲሱ ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብር እንደሚገልጸውሠነዱ በሰብአዊ መብቶች አያያዝና ጥበቃ ረገድ እስካሁን ከተገኘው መሻሻል የበለጠ ውጤት የሚያመጣ ነው። የአመለካከት ለውጥ እንዲፈጠር ለማድረግ ትምህርትና ሥልጠናን ለማስፋፋት ነጻ የግና የዳኝነት ሥርዓትን ለማጎልበትና የግ የበላይነትን በተሻለ ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ይሆናል።

ረቂቅ ሠነዱ በትህምርት፣ በጤና፣ በመኖሪያ ቤትና በማህበራዊ ዋስትና መስኮች መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ አመቺ ፖሊሲዎችንና ፕሮግራሞችን ቀርጾ ማስፈጸሚያ በጀት ለመመደብና ለመተግበር በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የፖለቲካ ፈቃደኝነትና ቁርጠኝነት ያለው አመራር መኖሩን ታሳቢ ያደረገ እንደሆነም ያሳያል። ረቂቅ የድርጊት መርሐ ግብሩ ተግባራዊ የሚደረገው በዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲጸድቅ ነው።
አዲስ ዘመን

No comments:

Post a Comment