Sunday, March 03, 2013

6ኛውን የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ በዓለ ሲመት ተካሄደ

(እሁድ, 03 መጋቢት, 2013, አዲስ አበባ)--የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 6ኛው ፓትሪያክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ሜቴያስ በዓለ ሲመት በካቴድራል ቅድስተ ስላሴ ቤተክርስቲያን የካቲት 24/2005ዓ.ም ተካሄደ



6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ሜቴያስ በዓለ ሲመት በቅድሰተ ሰላሴ ካቴድራል ሲካሄድ የተለያዩ ሀገራት እህት ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ እና ተወካዩች ተገኝተዋል።


ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ሜቴያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ቃለመሀላ ሲፈፅሙ

“እኔ አባ ማትያስ የካቲት 24 2005. የኢ////ክርስቲያን ፓትሪያክ ሆኜ ተሾሜያለሁ:: ስለዚህ የተጣለብኝን ሃላፊነት ያለምንም አድሎና ተፅዕኖ የኢ////ክርስቲያን ካህናት፤ ምዕመናንና ምዕመናት የሁሉም አባት ሆኜ በቅንነትና በታማኝነት፤ በፍቅርና በትህትና አገለግላለሁ”ብለዋል::

ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ቃለመሃላ ከፈጸሙ በኃላ እንዳሉት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ምዕመናን በሃይማኖት በስነ ምግባር ታንፀው እንዲኖሩ ለማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ በአንድ ልብ ይሰራል ። የቤተክርስቲያን አሰራር የበለጠ ተጠናክሮ መሄድ እንዳለበትም ገልጸዋል።

በ6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማቴያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ በዓለ ሲመት ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ የሃይማኖት ተቋማት በመቻቻልና በመከባበር እንዲሁም በማስተማር ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ርብርብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርትስቲያን የበኩሏን ሚና መወጣት እንዳለባት ተናግረዋል።

የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዩርጊስ በተወካዩቸው 6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ሜቴያስ ከወትሮ በበለጠ የሃይማኖት መቻቻል ለማጎልበት እና  ቤተክርስቲያኗ በልማት ስራዎች የምታካሂደው ጥረት ለማጠናከር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

No comments:

Post a Comment