Tuesday, October 02, 2012

ወደ አሜሪካ የሚያስገባው የዲቪ ሎተሪ ዛሬ መሞላት ተጀመረ

(Oct 02, 2012, Department of State)--የአሜሪካ መንግስት የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ወደ ሃገሩ ገብተው እንዲኖሩና እንዲሰሩ የሚፈቅድበት የዲቪ ሎተሪ ዛሬ ኦክቶበር 2 ቀን 2012 በኮምፒውተር መሞላት ጀመረ።  ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ያገኘችው መረጃ እንደሚያመለክተው የዲቪ 2014 (2014 Diversity Visa Program) ለአንድ ወር ያህል እስከ ኖቬምበር 3 ይሞላል።

ምናልባት የኢንተርኔት መስመር መጨናነቅ ስለሚኖር አመልካቾች እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ መጠበቅ የለባቸውም ያለው የስቴት ዲፓርትመንቱ ማሳሰቢያ በ እድሉ መጠቀም የሚፍልግ ካለ በጊዜ ማመልከቻውን መሙላት አለበት ብሏል።

ባንግላዲሽ፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቻይና፣ ኮሎምቢያ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኢኳዶር፣ ኤልሳልቫዶር፣ ሃይቲ፣ ሕንድ፣ ጃማይካ፣ ሜክሲኮ፣ ፓኪስታን፣ ፐሪ፣ ፊሊፒንስ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኢንግላንድ (ከሰሜን አየርላድ ውጭ)ና ቬትናም ባለፉት 5 ዓመታት ከ50 ሺህ ላይ ስደተኞች ወደ አሜሪካ ስለገቡ የ ዲቪ 2014 ባለ ዕድል ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ስቴት ዲፓርትመት አስታውቋል። የዲቪ ሎተሪ 2014ን ለመሙላት አድራሻው የሚከተለው ነው::  https://www.dvlottery.state.gov/ 

Related topic:

No comments:

Post a Comment