Tuesday, September 04, 2012

የኢትዮጵያ ህዝቦች የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ላሳዩት ጨዋነት መንግስት ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ ነሃሴ 29/2004 የኢትዮጵያ ህዝቦች የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ላሳዩት ጨዋነት የተሞላበት ሃዘን አገላለጽ ስነ ስርዓት የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስትና በድርጅታቸው ኢህዴግ ስም ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡ 

 
ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማሪያም ትናንት ምሽት በሰጡት መግለጫ ሁላችሁም መሪያችን ደህንነታቸው ተመልሶ ወደ ለመዱት ስራ እንዲመለሱ በከፍተኛ ደረጃ ተመኝታችኋል፣በተለያዩ ሃይማኖት አባቶችም አማካኝነት ጸሎት አድርጋችኋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ህልፈተ ህይወታቸው ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ አለምን ያስደነቀ የሃዘን መግለጫ ከጫፍ ጫፍ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ገደማ አከናውናችኋል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች በታሪካቸው መሪያቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ በታላቅ ፍቅር፣ ክብርና ሰላም በእንባ በታላቅ ስነ ስርዓትና ሞገስ መሸኘታቸውን አስታውቀዋል።

የአገራችን ህዝቦች የለፋላቸውንና የደከመላቸውን ሰው፣ ድርጅትና መንግስት ሚዛናዊና ምክንያታዊ ፍርድ የሚሰጡ መሆናቸውንና ኢትዮጵያ የታላቅ ህዝብ ሃገር መሆኗን ለወዳጅም ለጠላትም አስመስክራችኋል።

ዛሬ ወደፊታችሁ የቀረብኩት ስላደረጋችሁት ስለዚህ ታላቅ አለምን ያስደነቀ ስራችሁ የሚገባችሁን ምስጋና በድርጅታችን በኢህዴግና በኢፌድሪ መንግስት ስም በታላቅ አክብሮትና ትህትና ለማቅረብ ነው ያሉት ሚኒሰትሩ የከበረ ምስጋናቸውንም አድርሰዋል። Read more from ENA »

Related topics:
ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር የሚገኝ ቡድን እንደሚልኩ አስታወቁ

የኢትዮጵያና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሁለቱ አገራት ገለፁ 
Obama Speaks With Acting Ethiopian PM
Hailemariam, Ethiopia’s New Leader   
U.S. aid to Ethiopia helping neither us nor Ethiopians (CNN)
What’s Next for Ethiopia?     

No comments:

Post a Comment