Tuesday, September 04, 2012

የኢትዮጵያና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሁለቱ አገራት ገለፁ

(Sept 04, 2012, Addis Ababa)--ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ትናንት ማምሻውን በመንግሥታቱ ድርጅት የአሜሪካ ቋሚ ተወካይ በአምባሳደር ሱዛን ራይስ የተመራ የአሜሪካ ልዑክ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ አዲስ አበባ ነሃሴ 28/2012በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የቆየውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሁለቱ አገራት አስታወቁ፡፡ 

Susan  Rice and Acting prime minister Hailemariam Desalegne ( ENA)
አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የጀመረችውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የነደፈችው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን መሰረት ያደረገ ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደፊትም አሜሪካን ጨምሮ ከሌሎች አገራት በተጠናከረ መልኩ ይገፋበታል ብለዋል፡፡

አምባሳደር ሱዛን ራይስ በበኩላቸው ኢትዮጵያና አሜሪካ ታሪካዊ የሆነ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቀሰው ሁለቱ አገራት የጀመሩትን ስትራቴጂካዊ አጋርነት በላቀ ደረጃ እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል፡፡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ያላትን ቁርጠኛ አጋርነትም በተጨባጭ ማሳየት እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሶማልያ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የተጫወተችው ቁልፍ ሚና መልካም ውጤት እያሰገኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቅርቡ በሶማልያ ሠላማዊ የፓርላማ ምርጫ ተካሂዶ የአገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ መመረጡን አስታውሰው ለዚህ ታላቅ ወጤት መገኘት የኢትዮጵያ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የልማት እንቅስቃሴ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ያሳዩትን ከፍተኛ ፍላጎት በተቀናጀ አኳሃን ወደ ተግባር ለመለወጥ የአሜሪካን መንግሥት ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ምክንያት ከፍተኛ ኀዘን ውስጥ ቢሆኑም የዚች ታላቅ አገር ሕዝብ አንድነቱን በማጠናከር የተጀመረውን ልማት ዳር እንደሚያደርስ እርግጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በውይይቱም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የፖለቲካ ጉዳዮች አማካሪ ጌይል ስሚዝና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ጆን ካርሰን ተሳታፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Source: ENA

Related topics:
ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር የሚገኝ ቡድን እንደሚልኩ አስታወቁ
Obama Speaks With Acting Ethiopian PM
Hailemariam, Ethiopia’s New Leader  
U.S. aid to Ethiopia helping neither us nor Ethiopians (CNN)
What’s Next for Ethiopia?   

No comments:

Post a Comment