Sunday, September 09, 2012

መንግሥት በቅርቡ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ለኢንቨስተሮች ሊያቀርብ ነው

(Sept 08, 2012, Reporter)--መንግሥት በህዳር 2005 ዓ.ም. ውስጥ ሰፋፊና ለእርሻ የሚሆኑ መሬቶችን ለኢንቨስተሮች ማቅረብ እንደሚጀምር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡ መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት ሰፋፊ መሬቶችን ለተለያዩ የውጭና የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ሲሰጥ ቆይቶ፣ በ2004 ዓ.ም. አጋማሽ ላይ ሰፋፊ መሬት የወሰዱ ኩባንያዎችን የሥራ አፈጻጸም ለመገምገም በሚል ምክንያት መሬት ማቅረቡን አቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት ግምገማውን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኝ በመሆኑ፣ የመሬት አሰጣጥ ላይ ማሻሻያዎችን በማድረግ በመጪው ህዳር ወር ውስጥ የመሬት ጥያቄዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ አንድ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በተካሄደው ግምገማ የውጭም ሆኑ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች የወሰዱትን መሬት ሙሉ ለሙሉ በገቡት ውል መሠረት ማልማት አልቻሉም፡፡

በግምገማ መሠረት አንድ መቶ ሺሕ ሔክታር የወሰደ ኩባንያ ከሁለት ሺሕ ሔክታር በላይ አለማልማቱ ታውቋል፡፡ አሥር ሺሕ ሔክታር መሬት የወሰደውም ከአንድ ሺሕ ሔክታር መሬት ያልበለጠ መሬት ብቻ ነው እያለማ የሚገኘው ሲሉ ባለሥልጣኑ ለሪ

ከዚህ በተጨማሪም አብዛኛዎቹ ኩባንያዎች ደን እየመነጠሩ ከሰል በማክሰልና ጣውላ በማምረት ሕገወጥ ሥራዎች ላይ ተሰማርተዋል ተብሏል፡፡ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እኚሁ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን እንደገለጹት፣ መንግሥት ቆም ብሎ የኩባንያዎቹን የሥራ አፈጻጸም መገምገም አስፈልጎታል፡፡

ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ ኢንቨስተሮች ላይ ምን ዓይነት ዕርምጃ እንደሚወሰድ እስካሁን ያልተገለጸ ቢሆንም፣ መንግሥት በቸልታ የማያልፋቸው ኢንቨስተሮች መኖራቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በፌደራል መንግሥት ውሳኔ የግብርና ሚኒስቴር ከክልሎች ሰፋፊ የእርሻ መሬት በውክልና እየተረከበ ለኢንቨስተሮች ይሰጣል፡፡

በተለይ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል፣ ኦሮሚያና አማራ ክልሎች የግዙፍ ኩባንያዎች ትኩረት የሚስቡ የእርሻ መሬት ባለቤቶች እንደመሆናቸው በርካታ ኩባንያዎች በእነዚህ ክልሎች ቦታ ተረክበዋል፡፡
Source: Reporter

No comments:

Post a Comment