Friday, August 31, 2012

ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር የሚገኝ ቡድን እንደሚልኩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ነሃሴ 25/2004)-- የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኝ የልዑካን ቡድን ዛሬ ይፋ አደረጉ። 

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የፕሬዝዳንቱ ልዑካን በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ ቋሚ ተወካይ በአምባሳደር ሱዛን ራይስ መሪነት ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም በሚፈጸመው ሥርዓተ ቀብር ላይ ይገኛል።

የፕሬዝዳንቱ ልዑካን አባላትም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ቡዝ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ጆኒ ካርሰን እና የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪና የብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ዳይሬክተር ሚስ ጋይሌ ስሚዝ ናቸው። 
Source: ENA

No comments:

Post a Comment