Saturday, August 18, 2012

አቡነ ቤኒዲክት 16ኛ በአቡነ ጳውሎስ ሞት የተሰማቸውን ኅዘን ገለጹ

(አዲስ አበባ ነሐሴ 12/2004)--የሮማው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቤኒዲክት 16ኛ በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጳውሎስ ሞት የተሰማቸውን ኅዘን ገለጹ። 

Pope Benedict XVI
አቡነ ቤኒዲክት 16ኛ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ባስተላለፉት የኅዘን መግለጫ በፓርትያርኩ ድንገተኛ ሞት ጥልቅ ኅዘን እንደተሰማቸው በቤተ ክርስቲያናቸው ስም ገልጸዋል።ለእምነቱ ተከታዮችም መጽናናትን ተመኝተዋል።

''አቡንነታቸው በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግንኙነትና ወዳጅነት እንዲጠናከር ያደረጉት ጥረትም የሚደነቅ ነው'' ብለዋል።

አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ላለፉት 20ዓመታት የመሯት ሲሆን፣በታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች ሳይቀር የእምነት ተቋማት ለሰላም መከበር በጋራ እንዲሰሩ ጥረት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ፓትርያርኩ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን የአፍሪካ ስደተኞችን ለመርዳት ባደረጉት እንቅስቃሴ ''ናንሰን'' የተባለውን ሜዳሊያ ሸልሟቸዋል።
በቅርቡ ደግሞ ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ላደረጉት አስተዋጽኦ ዓለም አቀፍ ሽልማት ተቀብለዋል። አቡነ ጳውሎስ ከዚህች ዓለም በሞት የተለዩት በ76ዓመታቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። 

Source: ENA

Related topics:
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ አረፉ።  
Abune Paulos Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church dies
 Home

No comments:

Post a Comment