(June 17, 2012, Reporter)--የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አወዛጋቢውን የሊዝ አዋጅ የሚያስፈጽሙ ደንብና መመርያ አፀደቀ፡፡
የከንቲባ ጽሕፈት ቤት የፀደቁትን ደንብና መመርያ ካለፈው ሐሙስ ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚመለከታቸው የአስተዳደሩ መሥርያ ቤቶች አሰራጭቷል፡፡
ደንብና መመርያው የደረሱዋቸው የየመሥርያ ቤቱ ባለሥልጣናትና የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች የፀደቁትን ደንብና መመርያ መሰንበቻውን ሲመረምሩ ቆይተዋል፡፡
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በፀደቁት ደንብና መመርያ ላይ ጥያቄዎች በመነሳታቸው፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ለሚመለከታቸው አካላት ማብራርያ ለመስጠት ለማክሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. ስብሰባ ጠርቷል፡፡
የከተማው አስተዳደር ደንብና መመርያውን ያዘጋጀው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረትና በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የወጣውን ሞዴል ደንብ መነሻ በማድረግ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ይህንን ሞዴል ደንብ አዲስ አበባንና ድሬደዋ ከተማን ጨምሮ ለዘጠኙም ክልሎች ማሰራጨቱ ይታወሳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ የመሬት ሥሪት ባለሙያዎች በዚህ ሞዴል ደንብ ተመሥርተው ባለፉት ወራት ያረቀቁዋቸው ደንብና መመርያ ከሁሉም ክልሎች ቀደም ብሎ ፀድቀዋል፡፡ ምንጮቻችን እንደገለጹት፣ የድሬዳዋና የክልል አስተዳደር አካላት የየራሳቸውን ደንብና መመርያ በማዘጋጀት ሥራ ተጠምደዋል፡፡
በዓመቱ መጀመርያ ላይ የወጣው የከተማ ቦታን በሊዝ የመያዝ አዋጅም ሆነ በሚኒስቴሩ የተዘጋጀው ሞዴል ደንብ፣ በአምስት ዓመታት ውስጥ በሁሉም የክልል ከተሞች ውስጥ የሚገኝ መሬት ወደ ሊዝ ሥሪት እንደሚገባ ይደነግጋሉ፡፡
በተጨማሪም በዚህ ጊዜ ውስጥ ከውርስ በስተቀር ነባር ይዞታ ለሦስተኛ ወገን ሲተላለፍ ወደ ሊዝ ሥሪት ይገባል፡፡ ቦታው ወደ ሊዝ ሥሪት ሲገባ የዋጋው ስሌት በአካባቢው የሊዝ መነሻ ዋጋ ተመን መሠረት እንደሚስተናገድ ተደንግጓል፡፡
በወቅቱ እነዚህ አንኳር ጉዳዮች በኅብረተሰቡ ላይ ብዥታ በመፍጠራቸው በከፍተኛ ደረጃ ውዝግብ ማስነሳታቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ንብረት የማፍራት ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌን ይፃረራሉ፣ ኢንቨስትመንትን ይገድባሉ፣ ባንኮችን ለኪሳራ ይዳርጋሉ፣ ወዘተ የሚሉ የመቃወሚያ ሐሳቦች ከተለያዩ ወገኖች ቀርበዋል፡፡
በእነዚህ ነጥቦች ላይ ዘግይቶም ቢሆን በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባበሪነት በርካታ የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተዋል፡፡ በስብሰባዎቹም የሊዝ አዋጅን የሚቃወሙ ሐሳቦች ከመቅረባቸውም በተጨማሪ፣ የተለያዩ ግብዓቶች ለሚኒስቴሩ መቅረባቸው አይዘነጋም፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ አስተዳደር ያፀደቃቸው ደንብና መመርያ ሲያዘጋጁ ለሚኒስቴሩ የተሰጡ ግብዓቶች ያን ያህል እንዳልተጠቀመባቸው፣ ይልቁንም በአዋጁና በሞዴል ደንቡ ተመሥርቶ ደንብና መመርያውን እንዳዘጋጀ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
ከወራት በፊት ከሪፖርተር ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪና የኢሕአዴግ ምክር ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን የተነሱትን የመቃወሚያ ሐሳቦች አይቀበሏቸውም፡፡ በወቅቱ አቶ ሬድዋን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሊዝ አዋጁ መሠረት ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ሁሉም ዜጋ መጠቀም አለበት፡፡
“ኅብረተሰቡ አዋጁን በደንብ ቢረዳው በዓባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው የህዳሴ ግድብ ድጋፍ እንደሰጠው ሁሉ፣ ለሊዝ አዋጁም ሠልፍ ወጥቶ ድጋፉን ይሰጥ ነበር፤” ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በወጣው ደንብና መመርያ መሬት በዋናነት የሚሰጠው በጨረታ ሲሆን፣ ለከተማው ወሳኝ የሚባሉ ፕሮጀክቶችን የከተማው ካቢኔ ሊያየው እንደሚችል ተደንግጓል፡፡ የጨረታ ሒደቱ ቀደም ሲል በክፍላተ ከተሞች ኃላፊነት ሲካሄድ ቢቆይም፣ አዲሱ ደንብ በማዕከል ደረጃ ጨረታ እንዲወጣ ደንግጓል ሲሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ባፀደቃቸው ደንብና መመርያ ላይ የከተማው መሬት አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ቃሲም ፊጤ አስተያየት እንዲሰጡ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የሊዝ አዋጁ ማስፈጸሚያ የሆኑት ደንብና መመርያ መውጣታቸው ከተሰማ በኋላ በከተማው ውስጥ ሲካሄዱ የነበሩ የይዞታ ግብይቶች መቀዝቀዛቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይ ነባር ይዞታዎቻቸውን ለሦስተኛ ወገን የሚያስተላልፉ ግለሰቦችና በመሬት ላይ ያረፉ ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ወገኖች ደንቡና መመርያው ምን ዓይነት ዝርዝር ጉዳዮችን እንደያዙ ሳይረዱ ግብይት መፈጸም አለመፈለጋቸውን እየገለጹ ነው፡፡
Source: Reporter

No comments:
Post a Comment