(Sunday, 13 May 2012, Reporter)--በአዲስ አበባ ከተማ ለ22ኛ ጊዜ ከግንቦት 1 ቀን እስከ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. በተካሄደው የዓለም የኢኮኖሚ
ፎረም፣ የአፍሪካ መሪዎች በሙስና ውስጥ ለመዘፈቃቸው የውጪ ኢንቨስተሮች ተጠያቂዎች መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሐሙስ ከናሚቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነሀስ ጌዲዮን፣ ከናይጄሪያ
ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታንና ከጋቦን ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጐ ኦንዲምባ ጋር በመሆን ‹‹የአፍሪካ አመራር›› በሚል
ርዕስ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
እነዚህ አራት የአፍሪካ መሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ውይይት ላይ ጐባኖ ማንዳማራሶ የተባለች ደቡብ አፍሪካዊቷ ወጣት፣ ተሳታፊዎቹን ያስደመመ ጥያቄ ጠይቃለች፡፡ ወጣቷ፣ “በርካታ የአፍሪካ መሪዎች በወጣትነት ጊዜያቸው ባለራዕዮች ናቸው፡፡ ለአኅጉሪቷም አስገራሚ የሚባሉ ራዕዮች አሉዋቸው፡፡ ሆኖም በሥልጣን ወንበር ላይ ሲቀመጡ በመቅጽበት ይቀየራሉ፡፡ ስለዚህ በእነዚህ ወንበሮች ላይ ያለው መርዝ ምንድን ነው? እንዴትስ መከላከል እንችላለን?” ስትል ጥያቄዋን አቅርባለች፡፡
ደቡብ አፍሪካዊቷ ወጣት ላነሳችው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንዳሉት፣ በአፍሪካ ለሚታየው እንደዚህ ዓይነት ሙስና ስግብግብ የውጪ ኢንቨስተሮች ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ “በርካታ ጊዜ ባለራዕይ የነበሩ መሪዎች ወደተራ ሌብነት ሲገቡ አይተናል፡፡ እነዚህ የመንግሥት ባለሥልጣናት እየተከፈላቸውም ሆነ ሳይከፈላቸው አገራቸው ሲዘረፍ ተባባሪ ይሆናሉ፤” ብለዋል፡፡
ይህ የሚሆንበትን ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩ፣ “ትላልቅ የውጭ ኢንቨስተሮች ወደ አፍሪካ እንዲገቡ ለማድረግ ውስን የመደራደሪያ አቅም ነው ያለን፡፡ የእነሱ ወደ አፍሪካ መግባት ደግሞ የሥራ ዕድል ስለሚፈጥር አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ግን ስለአፍሪካ የሚወራው ነገር በጣም አስፈሪ ስለሆነ፣ እዚህ ገብቶ ሥራ ለመሥራት ያለው አደጋ በሰው ሠራሽ መንገድ አድጓል፡፡ በመሆኑም እነሱን ወደዚህ እንዲመጡ ለመሳብ ቀላል አይደለም፤” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ ዜጐች ከታችኛው እስከ ላይኛው የመንግሥት አካል ድረስ ሙስና እንዳይኖር የሚያስችል ከባቢ መፍጠር አለባቸው ብለዋል፡፡
የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት በበኩላቸው፣ በሁሉም የመንግሥት የሥልጣን ደረጃ ላይ ወጣቶች መምጣት አለባቸው ብለዋል፡፡ የጋቦኑ ፕሬዚዳንት ሴቶች ለአፍሪካ መለወጥ ጥሩ ዕድል ናቸው በማለት ተናግረዋል፡፡ አራቱም የአፍሪካ መሪዎች ታማኝነት፣ ራዕይ፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ለመሪዎች የሚያስፈልግ ባህሪ መሆኑን አስምረውበታል፡፡ የዓለም የኢኪኖሚ ፎረም መሥራችና ዋና ዳይሬክተር ክላውስ ሽዋብ፣ “አመራር አዕምሮ፣ ነፍስ፣ ልብና መልካም ነርቭ ሊኖሩት ይገባል፤” ብለዋል፡፡
ውይይቱም ሲጠናቀቅ የሽዋብ ፋውንዴሽን ስድስት አፍሪካዊ የሥራ ፈጣሪዎችን ሸልሟል፡፡ ኢትዮጵያዊቷ የሶል ሬብልስ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ቤቴልሔም ጥላሁን ከተሸላሚዎቹ መካከል መሆን ችላለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓለማችን ትልቁ የሸቀጣ ሸቀጥ አቅራቢ ኩባንያ ዎልማርት ለጊዜው በአፍሪካ ውስጥ አዲስ ገበያ እንደማይመሠርት አስታውቋል፡፡ የዎልማርት ዋና ዳይሬክተር ዳግ ማክሚላን እንዳሉት፣ ዎል ማርት አፍሪካ ውስጥ አሁን ባሉት 12 ገበያዎች ላይ ብቻ አተኩሮ ይሠራል፡፡ በመሆኑም ዎልማርት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንደማይገባም ታውቋል፡፡
የዎልማርት ዓመታዊ የሽያጭ ገቢው 450 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2010 ብቻ 14 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል፡፡ አሁን ያለው ከፍተኛ ግሽበት የተፈጠረው ወጥ ያልሆነ የገበያ ሥርዓት በአገሪቱ በመንገሱ ነው በማለት መንግሥት እንደ ዎልማርት ላሉ ትላልቅ ኩባንያዎች ጥሪ አድርጓል መባሉ ይታወሳል፡፡ የእነዚህ ኩባንያዎች ወደ አገሪቷ መግባት ግን በኢኮኖሚው ላይ ሌላ ችግር ይፈጥራል ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ቅጥ ያጣው የአገሪቱ የግብይት ሥርዓት በዘመናዊ ግብይት ካልተተካ በሕዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ቀውስ ይፈጠራል የሚሉ አሉ፡፡ የአገሪቱ የግብይት ሥርዓት ታንቆ የተያዘው በጥቂት የገበያው ተዋናዮች በመሆኑ ምክንያት ፍትሐዊ ግብይት ሊኖር ባለመቻሉ፣ እንደ ዎልማርት ያሉ ኩባንያዎች ገብተው ገበያው መረጋጋት አለበት የሚሉ ያመዝናሉ፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ሳትሆን ኢኮኖሚዋ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ፣ በርካታ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ዓይናቸውን እየጣሉባት እንደሚገኙ ዘ ኢኮኖሚስት ባወጣው ዘገባ አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ነዳጅ ከማያመርቱ አገሮች በኢኮኖሚ ዕድገት በቁንጮነት መቀመጧንም ገልጿል፡፡ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን ማዘጋጀት የቻለችው ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ብትሆንም፣ በመልካም አስተዳደርና በቢሮክራሲዋ አፋኝነት ምክንያት መልካም አጋጣሚዎች እንዳያመልጧት ከፎረሙ ጐን ለጐን በተካሄዱ ስብሰባዎች ተገልጿል፡፡ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም የአገሪቱን ገጽታ ለማሳደግ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ያዩት ተሳታፊዎች፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሊኖራት የሚገባትን ሚና ጠንክራ ማሳደግ ይገባታል ብለዋል፡፡ በተለይ በዲሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደርና በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ረገድ ያላትን ሪከርድ ማሻሻል ካልቻለች ልፋቷ ሁሉ ከንቱ ነው ተብሏል፡፡
ለሦስት ቀናት በቆየው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ዕድገት፣ መልካም አስተዳደር፣ የአፍሪካን ለውጥ መቅረጽ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚሉና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡ ከ700 በላይ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የዓለም አቀፍ ኩባንያ መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲዎችና በአፍሪካ ስማቸው የገነነ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እስከዛሬ ድረስ ነዳጅ ለማውጣት ሲደረግ የነበረው የመጨረሻው የነዳጅ ፍለጋ ሥራ፣ በያዝነው ዓመት መጨረሻ ወይም በሚቀጥለው ዓመት መጀመርያ ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ጠቆሙ፡፡
የሳውዝ ዌስት ኢነርጂ መሥራች ሊቀመንበርና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ አሸናፊ የውጤቱ የምሥራች አብሳሪ እንደሚሆኑ አያይዘው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ከመጡና ከፎረሙ በፊት በተካሄደው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለተሳተፉ ከ400 በላይ ለሚሆኑ የዓለም አቀፍ ኩባንያና የአገር ውስጥ ድርጅቶች ሥራ አስፈጻሚዎች፣ በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዳለ ባብራሩበት ወቅት ነው፡፡
ፕሪሳይስ ኮንሰልት በተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንዳብራሩት፣ በተለይ በማዕድን ፍለጋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብዙ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ባለሀብቶች ቢኖሩም፣ በዚሁ ዘርፍ ተጨማሪ የውጭ አገር ኢንቨስትመንት ለመሳብ አገሪቷ እንደምትፈልግ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በተከታታይ ባለሁለት አኅዝ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ስታስመዘግብ መቆየቷ፣ በቀላሉ ሊሠለጥን የሚችልና የፍጆታ ተጠቃሚ የሆነ ከ80 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት መሆኗ፣ ከዚህም በተጨማሪ የውጭ አገር ኢንቨስትመንት የሚስቡ የተለያዩ ማበረታዎች መኖራቸው፣ ኢትዮጵያን ለውጭ ኢንቨስትመንት አዋጪ አገር እንደማያደርጋት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርዋል፡፡
በማዕድን ፍለጋው ሰፊ የኢንቨስመንት ዕድል መኖሩን የጠቆሙት መለስ፣ በነዳጅ ፍለጋው መልካም ውጤቶች እንደሚኖሩ አመላክተዋል፡፡ አቶ ቴዎድሮስ በቅርቡ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች አገር እንደምትሆን እምነታቸው መሆኑን መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ኩባንያቸው በጋምቤላ፣ በጅማ ዙርያና በኦጋዴን በሦስት አካባቢዎች የነዳጅ ፍለጋ ሥራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ከነዳጅ ጋር በተያያዘ መልካም ዜና አብሳሪ እንደሚሆኑ የገለጹት አቶ ቴዎድሮስ፣ በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የተዘጋጀውን የዓለም ኢኮኖሚ ወፎረም ወደ በአፍሪካ ለማምጣት ለዓመታት ሲያደርጉ የነበረው እንቅስቃሴ በስተመጨረሻ እንደሰመረላቸው ለማየት ችለዋል፡፡
አቶ ቴዎድሮስ ለዓመታት ከኢትዮጵያ ብቸኛው የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም በአፍሪካ አባል እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡
Source: Reporter

No comments:
Post a Comment