(April 11, 2012, Reporter)--እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ሌሊት በካዲስኮ ሆስፒታል በ80 ዓመታቸው አረፉ፡፡
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ፋና ወጊ የሆኑት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሆስፒታል የገቡት ባለፈው እሑድ እንደነበረ የቅርብ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ሥርዓተ ቀብራቸውን በተመለከተ ጸሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ያሉበት ኮሚቴ እየመከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያመለክተው፣ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቅዳሜ ጥቅምት 12 ቀን 1925 ዓ.ም. በታሪካዊቷ አንኮበር ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1940 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ በመጓዝ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
ለስድስት አሠርት አቅራቢያ ያህል በሥነ ጥበብ ሥራዎቻቸው ገናና የነበሩት ሎሬት አፈወርቅ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በ1956 ዓ.ም. በሥነ ጥበብ የተሸለሙትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀዳጅተዋል፡፡
Source: Reporter
አፈወርቅ ተክሌ |

No comments:
Post a Comment