Monday, September 26, 2011

አራተኛው ብሔሪዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው

(መስከረም 15 ቀን 2004, አዲስ አበባ)--አራተኛው ብሔሪዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል በአዲስ አበባ ስታዲየም በደማቅ ስነስርዓት እየተከበረ ነው።

በበአሉ ላይ የፌዴሪ ኘሬዚዳንት ግርማ ወልደጊድርጊስ፣ የሕዝብ ተወካድች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት፣ የክልል ርእሰ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ሰራዊት አባላትም በበዓሉ ላይ ወታደራዊ ትርኢት ያሳዩ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ ማርሽ ባንድም የተለያዩ ጣእመ ዜማዎችን አሰምቷል።

አራተኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ''ሰንደቅ አላማችንና የሕዳሴው ግድብ ብሔራዊ ኩራታችን ናቸው።'' በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  

No comments:

Post a Comment