Thursday, August 30, 2018

የአየር ኃይል አውሮፕላን ተከስክሶ 17 ተሳፋሪዎች ሞቱ

(Aug 30, (FBC))--ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሆነ ዲኤች-6 አውሮፕላን ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ከረፋዱ አምስት ሰዓት ላይ ከድሬዳዋ ወደ ደብረ ዘይት አየር ኃይል ጠቅላይ መምርያ እየበረረ፣ ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ ናኖዋ ቀበሌ ውስጥ ተከስክሶ አብራሪዎቹን ጨምሮ 17 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡

የበረራ ቁጥር 808 የሆነው አውሮፕላን በአየር ላይ ሳለ እሳት ማሳየቱንና ደበጎጅ በተባለ ጫካ ውስጥ መከስከሱን የዓይን እማኞች የገለጹ ሲሆን፣ የአንድ ግለሰብ ማንነት ብቻ መለየት እንደተቻለ ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ከመከስከሱ በፊት እዛው አካባቢ ለማረፍ ሙከራ ማድረጉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን በቀለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
(ኤፍ.ቢ.ሲ)

No comments:

Post a Comment