Tuesday, September 26, 2017

የደመራ በዓል እየተከበረ ነው

(መስከረም 16፣2010, (በአዲስ አበባ  ))--የደመራ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው። በተለይም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ቅዱስ ባስልዮስን የእምነቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረጋላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ነው።

በዓሉ ባለፈው ዓመት በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ይታወሳል። በዚህም በበዓሉ ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ቁጥር እየጨመረ እንዲመጣ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል። የበዓሉ ስነስርዓት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቀጥታ ስርጭቶቹ  እያስተላለፈ ይገኛል። http://ethionetblog.blogspot.co.uk/p/etv-live.html
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment