Wednesday, February 22, 2017

አገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ይፋ ሆነ

(Feb 22, 2017, (EBC))--የኢንፎርሜሸን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በመንግሥትና በቁልፍ የግል ተቋማት የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሳይበር ደህንነት ስታንዳርድ አዘጋጀ፡፡

ስታንዳርዱ የመረጃ ደህንነት ሥጋቶችን ለመከላከል የሚያስችል አቅምንና ሂደቶችን እንዲገነቡ የሚያስችል ነው፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ እንደገለጹት "ሰነዱ የተቋማትን ኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን ስርዓት በማረጋገጥ ተቋማቱን ከተለያዩ የሳይበር ጥቃቶች ለመከላከል በሚችል መልኩ እንዲገነቡ የሚያስችል ነው"።

በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ መፍጠር ያለባቸውን አቅም በማሳደግ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሂደቶችን  ሰነዱ አጠቃሎ ይዟል።

No comments:

Post a Comment