(ጥቅምት 30፣ 2009, (ebc))--ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ለተመረጡት የሪፐብሊካኑን ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ መሪዎች የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት እየጎረፈላቸው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልካም እና ዉጤታማ የስራ ዘመንም ተመኝተዋል፡፡ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ዘመን ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንደሚል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ያላቸውን እምነት በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡
ዕድሜ ጠገቡ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና የንግድ ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም እምነታቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሩሲያውያው ፕሬዝዳንት ቭላድሜር ፑቲን የትራምፕ መመረጥ ሀገራቱ ከባላንጣነት ወጥተው በጋራ የሚሰሩበት ዘመን መምጣቱን ያሳያል ብለዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው እውነተኛው የእስራኤል ወዳጅ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማንም በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትን እንደሚያመጡ እምነት አለኝ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንት ሃሰን ሩሃኒ ደግሞ የትራምፕን መመረጥ የሀገሪቱን የውጭ ፖሊሲ ይቀይረዋል ብዬ አላምንም ሲሉ ስጋታቸውን አቅርበዋል፡፡
የቻናው ፐሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ትራንፕን እንኳን ደስ አለልዎት ካሉ በኋላ ውጤቱ ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መልካም እምርታ ያለው ነው ብለዋል፡፡ ጃፓን እና ተጎራባች ሀገሮችም ለትራምፕ እንኳን ደስ አልዎት እና የአብረን እንስራ መልዕክት አቅርበዋል፡፡
ከአፍሪካ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብጽ፣ ኮንጎ እና ሌሎችም ትራምፕን እንኳን ደስ አልዎት ብልዋል፡፡ የአሜሪካው የወቅቱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማም እንኳን ደስ አልዎት ካሉ በኋላ በመጪው ሀሙስ በዋይት ሀዉስ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:
Post a Comment