Thursday, May 02, 2013

የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ወደ ብሄራዊ ሙዚየም ተዛወረ

(ሚያዚያ 25/2005, (አዲስ አበባ))--በአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ የተነሳ የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት በግዜያዊነት ወደሚቆይበት ብሄራዊ ሙዚየም ዛሬ ሚያዚያ 25/2005 ተዛውሯል፡፡ ሃዉልቱ በነበረበት ቦታ የመሬት ዉስጥ የባቡር መስመር ይዘረጋል፡፡

 

የአዲስ አበባ የቀላል ባቡር ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር በሃይሉ ስንታየሁ እንዳሉት ሀዉልቱ አስካሁን በነበረበት መሬት ዉስጥ እስከ 20 ሜትር ጥልቀት በመቆፈር ስራዉ ይከናወናል፡፡ የዉስጥ ለዉስጥ ስራው እስከ መጭው ክረምት አጋማሽ ድረስ ተጠናቆ አፈር ይመለስበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ ስራው በተባለው ግዜ ሲጠናቀቅ የአደባባዩንና የመንገዱን ስራ በአዲስ መልክ በመገንባት ሃዉልቱ ወደ ነበረበት ቦታ በቀጣዩ አመት እንዲመለስ ይደረጋል ብሏል፡፡

ሀውልቱ በግዜያዊነት ሲነሳም ሆነ ወደፊት ወደቀድሞ ቦታው ሲመለስ ዉበቱን ከመጨመርና እስካሁን የተጎዱ የሀውልቱን ክፍሎች ከመጠገን ውጭ ምንም አይነት የቅርፅም ሆነ የይዘት ለዉጥ አይደረግበትም፡
ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት


No comments:

Post a Comment