Sunday, April 21, 2013

በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊውያን ወንዶች ድል ቀናቸዉ

(Apr 21, 2013, (አዲስ አበባ))--በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊውያን ወንዶች ድል ቀናቸዉ:: ከፍተኛ ግምት ባገኘው የለንደን ማራቶን የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው ፀጋዬ ከበደ በ2:06:03 ሰዓት አንደኛ በመውጣት አሸንፏል:: ኬንያዊው ኢማኑኤል ሙታይ ሁለተኛ ሲሆን ሌላዉ ኢትዮጵያዊ አየለ አብሽሮ ሶስተኛ ሆኗል::



ፈይሳ ሌሌሳም በአምስተኛነት ዉድድሩን አጠናቋል:: ፀጋዬ ከበደ በቤጂንግ ኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወሳል::

በሴቶቹ የማራቶን ዉድድር ኢትዮጵያዊወቹ አፀደ ባይሳና መሰለች መልካሙ አራተኛና አምስተኛ ወጥተዋል:: ያሸናፊነት ግምት አግኝታ የነበረችዉ ቲኪ ገላና በውድድሩ 15ኛ ኪሎ ሜትር ላይ የገጠማትን ግጭት ተቋቁማ ውድድሩን ብትቀጥልም ማሸነፍ ግን ሳትችል ቀርታለች:: ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ጄፕቶ ፕሪስካህ ነች::
ከኢሬቴድ 

Related topics:
ኃይሌ ፣ ቀነኒሳና ጥላሁን ድል ቀንቷቸዋል
 Home

No comments:

Post a Comment