Friday, March 08, 2013

ቤተክርስትያኗ የልማት ተሳትፎዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

(Mar 08, 2013, አዲስ አበባ)--የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በሀገሪቱ የሰላም፣የልማትና የዕድገት ጉዞ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ አጠናክራ እንደምትቀጥል ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ገለፁ፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ 6ኛውን የቤተክርስቲያኗ ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ብፁእነታቸው ቤተክርስትያኗ በሀገሪቱ የልማት ጉዞ በመሳተፍ ለሰላምና ለዕድገት የምታበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡

ምዕመኑም ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆንና በመከባበር በሀገሪቱ የልማት ተግባራት ላይ ተሳትፎውን እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በልማታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያላትን አስተዋፅኦ እንደምትቀጥል እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡

ወጣቱን በልማት ስራው በማሳተፍ እንዲሁም ከሀገር ወጥተው ወደ ዓረብ ሀገራት የሚሰደዱ ዜጎችን በማስተማር በኩል ትኩረት መሰጠት አለበትም ብለዋል፡፡ መንግስት ከቤተክርስትያኗ ጎን መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓትሪያሪኩ ገልፀውላቸዋል፡
 Home


No comments:

Post a Comment