Tuesday, October 30, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤተመንግሥት ገቡ

(Oct 30, 2012, VOA)--አቶ መለስ ዜናዊን በመተካት ከአምስት ሣምንታት በፊት ቃለ መሃላ የፈፀሙት  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ ወደ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት የታዘወሩት ከትላንትና በስቲያ ዕሁድ ነው። ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያድምጡ። 


አቶ ኃይለማሪያም ሥራቸውን ወዲያው የጀመሩት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀላቸው ጊዜአዊ ቢሮ እንደነበር ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ገልፀዋል።

ከሁሉም በላይ ትኩረት ስቦ የቆየው ግን ላለፉት አምስት ሣምንታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ ለመሥራት መገደዳቸው ነው።

ለዚህም ምክንያቱ የቀድሞዋ ቀዳሚት እመቤት አዜብ መስፍን ቤተመንግሥቱን ለቅቀው አለመውጣት እንደነበረ አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ጠቅሰዋል። አንድ የኢትዮጵያ መሪ ከቤተመንግሥት ውጭ ሲኖር አቶ ኃይለማሪያም የመጀመሪያው እንደሆኑ በመግለፅ የተቹም ነበሩ።
Source: VOA

No comments:

Post a Comment