Tuesday, August 21, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ

(አዲስ አበባ ነሐሴ 15/2004)--የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ትናንት ማታ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ባደረባቸው ሕመም በውጭ አገር ሕክምና ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ልማትና ዴሞክራሲ መፋጠንና ለአፍሪካ ህዳሴ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አርቆ አስተዋይ መሪ እንደነበሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በዓለም ዓቀፍ መድረኮችም ኢትዮጵያንና አፍሪካን በመወከል ለዓለም ዓቀፍ ሠላምና መረጋጋት መስፈን ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሰረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሆነው እንዲሰሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
Source: Ethiopian News Agency

Related topic:
Abune Paulos Patriarch of the Ethiopian Orthodox Church dies 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ አረፉ። 

No comments:

Post a Comment