Thursday, July 19, 2012

ሰበር ዜና፡ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕረፍት ላይ መሆናቸውን ገለጸ

(July 19, 2012, Reporter)--የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ  በዕረፍት ላይ መሆናቸውን ገለጸ፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያገጠማቸውን ቀላል የጤንነት ችግር ታክመው በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤና ችግር ምክንያት ባለባቸው ከፍተኛ የሥራ ጫና መሆኑን የገለጹት አቶ በረከት፣ በሐኪሞቻቸው ዕረፍት እንዲወስዱ መመከራቸውን ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የተሰጣቸውን የዕረፍት ጊዜ  አጠናቀው በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ተገልጻል፡፡

መንግሥት ስለ ጉዳዩ እስካሁን ለምን መግለጫ እንዳልሰጠ አቶ በረከት ሲገልጹ፣ እንደዚህ ዓይት ችግሮችን የኢሕአዴግ ፓርቲ ተቋቋሞ የማለፍ ባህል ስላለው ነው፡፡ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውንና በሥራ ጫና ምክንያት ካጋጠማቸው ሕመም አገግመው ወደ ሥራ እንደሚመለሱ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
Source: Reporter

No comments:

Post a Comment