Thursday, June 21, 2012

ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት የሚኖራት ስታዲየም

(ሰኔ 14/2004,ENA)--የፊፋንና የኦሎምፒክን ደረጃ በጠበቀ ሁኔታ እንደሚሠራ የተገለፀው አዲሱ የኢትዮጵያ ስታዲየም ግንባታው ከሁለት ዓመታት በኋላ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። በፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን አማካይነት በአዲስ አበባ የሚሠራው ስታዲየም 60 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ነው። 



ስታዲየሙ የስፖርት ውድድሮች ማካሄጃ ብቻ ሳይሆን የስፖርት መንደርም ይኖረዋል። ላቫ እና ዲዛይን ስፖርት የተባሉት ኩባንያዎች ጄዲኤደብልዩ ከተባለው አገር በቀል ኩባንያ ጋር በመተባበር ያቀረቡት ንድፍ ዓለም አቀፉን ውድድር አሸንፏል።
Source: ENA

No comments:

Post a Comment