Tuesday, March 13, 2012

ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሳዑዲ አረቢያ በሕክምና ላይ ናቸው

( መጋቢት 4 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) --የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሳዑዲ አረቢያ በሕክምና ላይ እንደሚገኙ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ ማምሻውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አንደገለጸው ፕሬዚዳንት ግርማ ከአሁን ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ የጤና ምርመራ ለማድረግ ባለፈው ሳምንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ የጤና ምርመራቸውን ጨርሰው ወደ አገራቸው እንደሚመለሱም የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡


Source: ENA

No comments:

Post a Comment