Tuesday, November 29, 2011

የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች አባቶች ተቃውሞ በግብረ-ሶዶማዊነት ላይ፤

(29.11.2011,Dw-world)--በ 16ኛው ዓለም አቀፍ የአባለ-ዘርእ በሽታዎች ጉባዔ ዋዜማ፣ ግብረ ሶዶማውያንየፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ፣ ጁፒተር ሆቴል፣ ሊያካሂዱ ያቀዱትን ጉባዔ፣ የሃይማኖት አባቶች በጽኑ ተቃውመውታል። አስተያየት ሰጪዎችም በበኩላቸው «ድርጊቱ መታሰቡ፤ በራሱ፤ አስጸያፊ ነው» ማለታቸው ተደምጧል።

የሃይማኖት አባቶች፣ ይህንን ጉዳይ፣ ጸያፍ፤ ከሥነ-ምግብር ውጭና ባህላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ  ነው በማለት ዛሬ ለዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ሊሰጡ የነበረው መግለጫ፤ እንዲሁም ለህዝቡ ሊያቀርቡት የነበረው ጥሪ ከጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ጋር ከመከሩ በኋላ፣ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጸዋል። Read more from Dw-world »

No comments:

Post a Comment