(አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ)--ኢትዮጵያና ፊንላንድ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከፊንላንድ አለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር ሄይዲ ሁዋታላ ጋር በጋራ የትብብሮሽ ጉዳዮች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው ይህ የተባለው።
የኢፊዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ፊንላንድ በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን ተደራሽነት ላይ ሰፊ ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች።
የፊንላንድ አለም አቀፍ የትብብር ሚኒስትር ሄይዲ ሁዋታላ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ፊንላንድ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ጨምረውም ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በሶማሊያ ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁ ሲሆን ሀገራቸው የጸጥታው ምክር ቤት አባል የምትሆን ከሆነ ይህን የኢትዮጵያን ጥረት እንደምትደግፍም ተናግረዋል።
ፊንላንድ በጸጥታው ምክር ቤት መቀመጫ እንዲኖራት ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ይህ ጥያቄዋም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተቀባይነት ማግኘቱን የባልደረባችን ታደሰ ብዙአለም ዘገባ ያመለክታል።
Source: ኤፍ ቢ ሲ

No comments:
Post a Comment