(ጳጉሜን 2 ቀን 2003 (አዲስ አበባ, ኢዜአ)--በለንደን የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ ለትምህርት ቤት ግንባታ ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በዝግጅቱ ላይ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዢ ተፈጽሟል።
በአማራ ክልል ለቦሰና ወረዳ ገፊት ቆላ ቀበሌ ትምህርት ቤት ማሰሪያ የሚውል ከ120 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡንም ገልጿል።
በለንደን የኢፌዲሪ ኤምባሲ ምክትል መሪ አምባሳደር አብዲረሺድ ዱለኔ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያውያን በክልሎቻቸው የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን ለመደገፍ ያሳዩትን መነሳሳት አድንቀዋል።
በለንደን የሚገኘው አልማ በአማራ ክልል ቦሰና ወረዳ ገፊት ቆላ ቀበሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማሰራት ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር የሚያደርገውን እንቅስቃሴም አመስግነዋል።
መንግስት የአምሰት ዓመቱን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት በተለይ በትምህርት ዘርፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።
ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር የአገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን ከሚያደርጉት ርብርብ ጎን ለጎን የህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል።
ከ ኢትዩዽያ ዜና አገልግሎት

No comments:
Post a Comment